ወደ ንጉሡም ቤት ወደ ጸሓፊው ክፍል ወረደ፤ እነሆም አለቆቹ ሁሉ፥ ጸሓፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ፥ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
ኤርምያስ 36:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ንጉሡም ወደ አደባባይ ገቡ፥ ክርታሱንም በጸሓፊው በኤሊሳማ ክፍል አኑረውት ነበር፤ ቃሉንም ሁሉ ለንጉሡ ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብራናውን ጥቅልል በጸሓፊው በኤሊሳማ ክፍል ካስቀመጡት በኋላ፣ ንጉሡ ወዳለበት አደባባይ ሄደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክርታሱንም በጸሐፊው በኤሊሳማ ጓዳ አስቀምጠው ወደ ንጉሡ አደባባይ ገቡ፤ ቃሎቹንም ሁሉ በንጉሡ ጆሮ ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለ ሥልጣኖቹም የብራናውን ጥቅል በጸሐፊው በኤሊሻማዕ ክፍል አኖሩት፤ ወደ ንጉሥም አደባባይ ሄደው የሆነውን ነገር ሁሉ አሳወቁት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ንጉሡም ወደ አደባባይ ገቡ፥ ክርታሱንም በጸሐፊው በኤሊሳማ ጓዳ አኑረውት ነበር፥ ቃሉንም ሁሉ በንጉሡ ጆሮ ተናገሩ። |
ወደ ንጉሡም ቤት ወደ ጸሓፊው ክፍል ወረደ፤ እነሆም አለቆቹ ሁሉ፥ ጸሓፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ፥ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
ንጉሡም ክርታሱን ያመጣ ዘንድ ይሁዳን ላከ፤ እርሱም ከጸሓፊው ከኤሊሳማ ክፍል ወሰደው፤ ይሁዳም በንጉሡና በንጉሡ አጠገብ በቆሙት አለቆች ሁሉ ጆሮ አነበበው።