ኤርምያስ 36:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚክያስም ባሮክ በሕዝቡ ጆሮ በመጽሐፉ በአነበበ ጊዜ የሰማውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሮክ ለሕዝቡ ከብራናው ሲያነብብ ሚክያስ የሰማውን ሁሉ ከነገራቸው በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚክያስም ባሮክ መጽሐፉን በሕዝቡ ጆሮ ባነበበ ጊዜ የሰማውን ቃላት ሁሉ ነገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚክያስም ባሮክ ለሕዝቡ ሲያነብላቸው የሰማውን ቃል ሁሉ ነገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚክያስም ባሮክ በሕዝቡ ጆሮ በመጽሐፉ ባነበበ ጊዜ የሰማውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። |
ልብህን አላደነደንህምና፥ እነርሱም ለጥፋትና ለመርገም እንዲሆኑ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የተናገርሁትን ሰምተህ በእግዚአብሔር ፊት ተዋርደሃልና፥ ልብስህን ቀድደሃልና፥ በፊቴም አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ በይሁዳ ንጉሥ ፊት በተነበበው መጽሐፍ የተጻፉትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገርን አመጣለሁ፥
ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ።