ኤርምያስ 35:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬካባውያንም ልጆች ፊት የወይን ጠጅ የሞላባቸውን ማድጋዎችንና ጽዋዎችን አኑሬ፥ “የወይኑን ጠጅ ጠጡ” አልኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሬካባውያንም ሰዎች ፊት በወይን ጠጅ የተሞሉ ማድጋዎችን አቀረብሁ፤ ዋንጫዎችንም ሰጥቻቸው፣ “በሉ፤ የወይን ጠጅ ጠጡ” አልኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በሬካባውያን ልጆች ፊት የወይን ጠጅ የሞላባቸውን ማድጋዎችንና ጽዋዎችን አስቀምጬ፦ “የወይኑን ጠጅ ጠጡ” አልኳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወይን ጠጅ የተሞሉ ማንቈርቈርያና ጽዋዎችን በሬካባውያን ፊት አስቀምጬ “እስቲ የወይን ጠጅ ጠጡ” አልኳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬካባውያንም ልጆች ፊት የወይን ጠጅ የሞላባቸውን ማድጋዎችንና ጽዋዎችን አኑሬ፦ የወይኑን ጠጅ ጠጡ አልኋቸው። |
“ወደ ሬካባውያን ቤት ሄደህ ተናገራቸው፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት አምጥተህ ከክፍሎቹ ወደ አንዲቱ አግባቸው፤ የወይን ጠጅም አጠጣቸው።”
“እናንተ ግን ለእኔ የተለዩትን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ ነቢያቱንም፥ “ትንቢትን አትናገሩ ብላችሁ ከለከላችኋቸው።