ኤርምያስ 33:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለምሽግና ለመከላከያ ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከባቢሎናውያን ጋራ ባለው ውጊያ፣ ዐፈር በመደልደልና በሰይፍ የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶችና ስለ ይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት እንዲህ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰይፍ ፊትና ከከበባት የአፈር ድልድል ለመከላከል ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላልና፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከበባውና በጦርነቱ ጥቃት ምክንያት የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ቤተ መንግሥት ይፈራርሳሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦ |
የበለጸገች ከተማና ቤቶችዋ ምድረ በዳ ይሆናሉ። የከተማውን ሀብትና ያማሩ ቤቶችን ይተዋሉ፤ አንባዎችም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማሪያ ይሆናሉ።
አሕዛብም መጥተው ይህችን ሀገር ያዟት፤ ይህችም ከተማ ከረኃቡና ከጦሩ የተነሣ በወጓት በከለዳውያን ሰዎች እጅ ወደቀች፤ እንደ ተናገርኸውም ሆነ።
ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ኀይልን አፍስሱ ይህች ከተማ የሐሰት ከተማ ናት፤ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።
ዛይ። እግዚአብሔር መሠዊያውን ጣለ፤ መቅደሱንም ጠላው፤ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ድምፃቸውን በዕልልታ አሰሙ።
የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ምዋርት በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።
እርሱ በምድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ ጠባቂዎችንም በአንቺ ላይ ያስቀምጣል፤ በዙሪያሽም ግንብ ይሠራል፤ የጦር መሣሪያም ይዘው ይከቡሻል፤ በጦራቸውም ይወጉሻል፤
በውስጧም የሚዋጉበት ግንብን ሥራ፤ በሠራዊትም ክበባት፤ በዙሪያዋም ጦር አስፍር፤ የሚዋጋ ጦርንም ወደ አደባባይዋ ላክ።
ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፤ ትቈርጣቸውማለህ፤ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ።