La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 33:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት በም​ት​ሉ​አት በዚች ስፍራ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው በሌለ፥ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ባድማ በሆኑ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህችን ስፍራ፣ “ሰውና እንስሳት የማይኖሩባት ባድማ ናት” ትላላችሁ፤ ነገር ግን ሰውም ሆነ እንስሳ ባልነበሩባቸውና ባድማ በሆኑት በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች፣ እንደ ገና ድምፅ ይሰማል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናንተ፦ ‘ያለ ሰውና ያለ እንስሳ የሆነች ባድማ ናት’ በምትሉአት በዚህች ስፍራ፥ ሰውም በማይቀመጥባቸው፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ላይ ዳግመኛ ይህ ይሰማል

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ‘ይህች ምድር ሰዎችም ሆኑ እንስሶች የማይኖሩባት ባድማ ነች’ ያልከው አባባል ለጊዜው ትክክል ነው፤ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም መንገዶች ምንም ሰዎች ወይም እንስሶች የማይታዩባት ባድማ ነች፤ አንድ ቀን ግን በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ ድምፅ ይሰማል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፥ የሚቀመጥባቸው በሌላ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 33:10
9 Referencias Cruzadas  

ትሰ​ማ​ኛ​ለ​ህና በመ​ከ​ራዬ ቀን ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም፥ “ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆ​ናል፤ ይችም ከተማ ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ኖ​ር​ባ​ትም የለም ብለህ ስለ ምን ትን​ቢት ተና​ገ​ርህ?” ሕዝ​ቡም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ተሰ​ብ​ስ​በው ነበር።


አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ስለ እር​ስዋ፥ “በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች ስለ​ም​ት​ላት ከተማ እን​ዲህ ይላል፦


እና​ን​ተም፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች በም​ት​ሉ​አት ምድር እር​ሻን እንደ ገና ይገ​ዛሉ።


እነሆ እኔ አዝ​ዛ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ሀገር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ጋሉ፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው የሌ​ለ​በት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥ​ን​ቶ​ቻ​ችን ደር​ቀ​ዋል፤ ተስ​ፋ​ች​ንም ጠፍ​ቶ​አል፤ ፈጽ​መ​ንም ተቈ​ር​ጠ​ናል ብለ​ዋል።


ምድ​ሪ​ቱ​ንም የተ​ፈ​ታች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ር​ስዋ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ቃሉ።


በውኑ ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በተሸለሙ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?