እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸክላ ሠሪ የሠራውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤
ኤርምያስ 32:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠበቅ ዘንድ የታተመውን ይህን የውል ወረቀት ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የታሸገውንና ያልታሸገውን፣ ሁለቱን የግዥ ውል ሰነዶች ለብዙ ጊዜ ሳይበላሹ እንዲቈዩ ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ተጠብቀው እንዲቆዩ የታተመውን ይህን የተገዛበትን የውል ሰነድና ካልታተመው የውል ሰነድ ጋር በአንድ ላይ ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የታሸገውንና ግልጥ የሆነውን ሁለቱንም የሽያጭ ውል ወረቀት ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ እንድታኖረውና ለብዙ ዘመን ተጠብቆ እንዲኖር አድርግ፤’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠበቁ ዘንድ የታተመውንና የተከፈተውን ይህን የውል ወረከት ወስደህ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸክላ ሠሪ የሠራውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”