ኤርምያስ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፦ ወደ እኔ ተመለሽ አልኋት፤ ነገር ግን አልተመለሰችም፤ አታላይ እኅቷ ይሁዳም አየች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፤ ሆኖም አልተመለሰችም፤ ከሓዲዋ እኅቷ ይሁዳም ይህን አየች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ ወደ እኔ ትመለሳለች’ ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም፤ አታላይ እኅትዋም ይሁዳ አየች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እንደገና ወደ እኔ የምትመለስ መስሎኝ ነበር፤ እርስዋ ግን አልተመለሰችም፤ እምነት የማይጣልባት የእርስዋ እኅት ይሁዳም ይህን ሁሉ አይታለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፦ ወደ እኔ ትመለሳለች ብዬ ነበር፥ ነገር ግን አልተመለሰችም፥ አታላይ እኅትዋም ይሁዳ አየች። |
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል?
“ይህ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል፥ እንዲሁ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል ያለውን ነገር አትመለከትምን?
ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፤ ታናሽቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።
አንቺ ግን በመንገዳቸው አልሄድሽም፤ እንደ ኀጢአታቸውም አላደረግሽም፤ ያው ለአንቺ ጥቂት ነበረና በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የሚከፋ ኀጢአት አደረግሽ።
ሰማርያ በአምላክዋ ላይ ዐምፃለችና ፈጽማ ትጠፋለች፤ በሰይፍም ይወድቃሉ፤ ሕፃኖቻቸውንም ይጥሉአቸዋል፤ እርጉዞቻቸውንም ይሰነጥቋቸዋል።
የሁለት ወይም የሦስት ከተሞች ሰዎች ወደ አንዲት ከተማ ውኃ ይጠጡ ዘንድ ሄዱ፤ ነገር ግን አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።