ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባቶቻቸው ኀጢአት ተመለሱ፥ ያመልኩአቸውም ዘንድ እንግዶችን አማልክት ተከተሉ፤ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
ኤርምያስ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ከጎስቋላዋ ይሁዳ ይልቅ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ራስዋን አጸደቀች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ከከሓዲዋ ይሁዳ ይልቅ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ጻድቅ ሆና ተገኘች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታም እንዲህ አለኝ፦ ከአታላይቱ ከይሁዳ ይልቅ ከዳተኛይቱ እስራኤል ጸደቀች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ እስራኤል ከእርሱ ብትለይ፥ እምነት ከማይጣልባት ከይሁዳ የምትሻልበት መንገድ መኖሩን እግዚአብሔር ነገረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ከአታላይቱ ከይሁዳ ይልቅ ከዳተኛይቱ እስራኤል ጸደቀች። |
ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባቶቻቸው ኀጢአት ተመለሱ፥ ያመልኩአቸውም ዘንድ እንግዶችን አማልክት ተከተሉ፤ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
“ከዳተኞች ልጆች ሆይ! ተመለሱ፤ ቍስላችሁንም እፈውሳለሁ። እነሆ እኛ አገልጋዮችህ እንሆናለን፤ አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና።
ከዳተኛዪቱም እስራኤል እንዳመነዘረች አየሁ፤ የፍችዋንም ደብዳቤ በእጅዋ ሰጥቼ ሰደድኋት፤ ጎስቋላ እኅቷ ይሁዳ ግን በዚያ አልፈራችም፤ እርስዋም ደግሞ ሄዳ አመነዘረች።
አንቺ ግን በመንገዳቸው አልሄድሽም፤ እንደ ኀጢአታቸውም አላደረግሽም፤ ያው ለአንቺ ጥቂት ነበረና በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የሚከፋ ኀጢአት አደረግሽ።
“እኅቷም ሐሊባ ይህን አየች፤ ሆኖም ከእርስዋ ይልቅ በፍቅር በመከተልዋ ረከሰች፤ ዝሙቷንም ከእኅቷ ዝሙት ይልቅ አበዛች።