እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
ኤርምያስ 29:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፤ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፤ ተጋቡ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፤ አትክልት ተክላችሁ ፍሬውን ብሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቶችን ሠርታችሁ ተቀመጡ፤ አታክልትም ትከሉ፤ ፍሬዋንም ብሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ቤት ሠርታችሁ ኑሩ፤ አትክልት ትከሉ፤ ፍሬውንም ብሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፥ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
እርሱ፦ ምርኮው የረዘመ ነውና ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፤ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአልና።”
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ፤ ጥቂቶችም አትሁኑ።
ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይኑንም ይተክላሉ፤ በዙሪያቸውም በአሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን በአደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው፥ የአባቶቻቸውም አምላክ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።