እረኞች አእምሮአቸውን አጥተዋልና፥ እግዚአብሔርንም አልፈለጉትምና፤ ስለዚህም መሰማሪያውን አላወቁም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
ኤርምያስ 23:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በማሰማሪያ ቦታዬ ያሉትን በጎቼን ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔር መንጋ የሆነውን ሕዝብ ለሚበትኑና ለሚያጠፉ መሪዎች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር። |
እረኞች አእምሮአቸውን አጥተዋልና፥ እግዚአብሔርንም አልፈለጉትምና፤ ስለዚህም መሰማሪያውን አላወቁም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፤ እድል ፈንታዬንም አርክሰዋል፤ የምወድዳትንም እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገዋታል።
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፤ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች፥ እነርሱና ንጉሦቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ካህናቶቻቸውም፥ ነቢያቶቻቸውም ያፍራሉ።
ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፤ ሕጌን የተማሩትም አላወቁኝም፤ ጠባቂዎችም ዐመፁብኝ፤ ነቢያትም በበዐል ትንቢት ተናገሩ፤ የማይጠቅማቸውንም ነገር ተከተሉ።
በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይወስዳቸዋል፤ ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ፤ በወዳጆችሽም ፊት ቷረጃለሽ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፥ “በጎችን በትናችኋል፤ አባርራችኋቸውማል፥ አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ! እንደ ሥራችሁ ክፋት እጐበኛችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።
“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፤ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ዐለፉ፤ በረታቸውንም ረሱ።
እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻ ስለምትገፉአቸው፥ የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው፥
እንደ ተቀደሱ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዶአል፥ አውራ ፍየሎችንም እቀጣለሁ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።
ሌባ ግን ሊሰርቅና ሊያርድ፥ ሊያጠፋም ካልሆነ በቀር አይመጣም፤ እኔ ግን የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኙ፥ እጅግም እንዲበዛላቸው መጣሁ።
ጠባቂ ያይደለ፥ በጎቹም ገንዘቡ ያይደሉ ምንደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም መጥቶ በጎችን ይነጥቃቸዋል፥ ይበትናቸዋልም።