La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 2:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ድረ በዳ ባሉ ውኃ​ዎች ተዘ​ረ​ጋች፤ በሰ​ው​ነ​ቷም ምኞት ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ይይ​ዟ​ታል፤ የሚ​መ​ል​ሳት ግን የለም፤ የሚ​ሹ​አ​ትም አይ​ደ​ክ​ሙም፤ በተ​ዋ​ረ​ደ​ች​በ​ትም ጊዜ ያገ​ኙ​አ​ታል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣ በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤ ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል? ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፤ ከጋለው ምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በበረሓ መኖርን የለመደች የሜዳ አህያ፥ ፍትወት በተቀሰቀሰባት ጊዜ ማን ሊቈጣጠራት ይችላል? ወንዶች የሜዳ አህዮች ያሉበትን ስፍራ፥ ራስዋ አነፍንፋ ስለምትደርስበት፥ እነርሱ እርስዋን በመፈለግ መድከም አያስፈልጋቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፥ ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 2:24
8 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በከ​ንቱ ነገ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ሰው፥ ከሴ​ትም የሚ​ወ​ለድ ሟች የሜዳ አህ​ያን ይመ​ስ​ላል።


እር​ስዋ የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ት​ንስ ሙሉ ወራት ትቈ​ጥ​ራ​ለ​ህን? ከም​ጥስ ትገ​ላ​ግ​ላ​ታ​ለ​ህን?


የሜዳ አህ​ዮ​ችም በወና ኮረ​ብታ ላይ ቆመ​ዋል፤ እንደ ሰገ​ኖም ወደ ነፋስ አለ​ከ​ለኩ፤ ሣርም የለ​ምና ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ጠወ​ለጉ።


ግን​ዱን፥ “አንተ አባቴ ነህ፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም፦ አንተ ወለ​ድ​ኸኝ” ይላሉ፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡኝ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ግን፥ “ተነ​ሥ​ተህ አድ​ነን ይላሉ።


ለአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዎች ሁሉ ዋጋ ይሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ አንቺ ግን ለወ​ዳ​ጆ​ችሽ ሁሉ ዋጋ ትሰ​ጫ​ለሽ፤ ከአ​ን​ቺም ጋር ለማ​መ​ን​ዘር በዙ​ሪ​ያሽ ይገ​ቡ​ብሽ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ትሰ​ጫ​ቸ​ዋ​ለሽ።


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


ለብ​ቻ​ውም እን​ደ​ሚ​ቀ​መጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም እንደ ገና ለመ​ለመ፤ እጅ መን​ሻ​ንም ወደደ።