ኤርምያስ 17:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዳ አትሁንብኝ፤ በክፉም ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስደንጋጭ አትሁንብኝ፤ በመከራ ቀን መሸሸጊያዬ አንተ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለማስፈራራት አትሁንብኝ፤ በመከራ ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ በመከራ ጊዜ መሸሸጊያዬ ስለ ሆንክ አስደንጋጭ አትሁንብኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለማስፈራራት አትሁንብኝ፥ በመከራ ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ። |
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
አቤቱ! የእስራኤል ተስፋ ሆይ! የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።
እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ይራራል፤ የእስራኤልንም ልጆች ያጸናል።