ኤርምያስ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕመሜ ለምን ጸናብኝ? ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ? እንደሚያታልል ወንዝ፣ እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕመሜ የማይድነው፥ ቊስሌስ የማይጠገነውና የማይፈወሰው ለምንድን ነው? በበጋ ወራት እንደሚደርቅ ጅረት ተስፋ ታስቈርጠኛለህን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆነኛለህን? |
በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ጠልታታለችን? ስለ ምን መታኸን? ፈውስስ ስለ ምን የለንም? ስለ ምን ተስፋ አደረግን? ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም፤ የፈውስን ጊዜ ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ድንጋጤ ሆነ።
ታላላቆችዋም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድጓድ መጡ፤ ውኃም አላገኙም፤ ዕቃቸውንም ባዶውን መለሱ፤ ዐፈሩም፤ ተዋረዱም፤ ራሳቸውንም ተከናነቡ።
ቍስልህ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ ይህን አድርጌብሃለሁ።