ጌታ ሆይ! አስታውቀኝ፤ እኔም አውቃለሁ፤ ያንጊዜም ሥራቸውን ገለጥህልኝ።
እግዚአብሔር ስውር ዕቅዳቸውን ገለጠልኝ፤ እኔም ዐወቅሁ፤ በዚያ ጊዜ ሥራቸውን አሳይቶኝ ነበርና።
ጌታም አስታወቀኝ እኔም አወቅሁ፤ ሥራቸውንም ገለጥህልኝ።
በዚያን ጊዜ እነርሱ የሚያደርጉትን ነገር እግዚአብሔር ስላሳየኝ ሤራቸውን ዐወቅሁት።
እግዚአብሔርም አስታወቀኝ እኔም አወቅሁ፥ ሥራቸውንም ገለጥህልኝ።
ኤልሳዕ ግን በቤቱ ተቀምጦ ነበር፤ ሽማግሌዎችም ከእርሱ ጋር ተቀምጠው ነበር፤ ንጉሡም በፊቱ ከሚቆሙት አንድ ሰው ላከ፤ መልእክተኛውም ገና ሳይደርስ ለሽማግሌዎች፥ “ይህ የነፍሰ ገዳይ ልጅ ራሴን ይቈርጥ ዘንድ እንደ ላከ እዩ፤ መልእክተኛውም በመጣ ጊዜ ደጁን ዘግታችሁ ከልክሉት፤ በደጅም ይቆም ዘንድ ተዉት፤ የጌታው የእግሩ ኮቴ በኋላው ነው” አላቸው።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
ማንም አንዳች ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልጉታል፤’ በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል።”
የእግዚአብሔር እውነት በእኔ ሐሰተናነት ለክብሩ ከፍ ከአለ እንግዲህ እኔን እንደ ኀጢአተና ለምን ይፈርድብናል?