ርብቃም ከእርስዋ ዘንድ በቤት የነበረውን የታላቁን ልጅዋን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፤ ለታናሹ ልጅዋ ለያዕቆብም አለበሰችው፤
ያዕቆብ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድኻ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወርቅ ቀለበት ያደረገና ያማረ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢመጣ እንዲሁም ያደፈ ልብስ የለበሰ ድኻ ሰው ቢገባ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወርቅ ቀለበት ያደረገና ያማረ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤያችሁ ቢመጣ እንዲሁም ያደፈ ልብስ የለበሰ ድኻ ሰው ቢገባ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምሳሌ ሁለት ሰዎች ወደምትሰበሰቡበት ቦታ ይመጣሉ፤ አንደኛው በጣቱ የወርቅ ቀለበት ያደረገና የሚያምር ጌጠኛ ልብስ የለበሰ ሀብታም ነው፤ ሌላው ያደፈ አሮጌ ልብስ የለበሰ ድኻ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወርቅ ቀለበት ያደረገና የጌጥ ልብስ የለበሰ ሰው ወደ ጉባኤአችሁ ቢገባ፥ እድፍ ልብስም የለበሰ ድሀ ሰው ደግሞ ቢገባ፥ |
ርብቃም ከእርስዋ ዘንድ በቤት የነበረውን የታላቁን ልጅዋን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፤ ለታናሹ ልጅዋ ለያዕቆብም አለበሰችው፤
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።
አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ያማሩ ልብሶችን ቶሎ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱም ቀለበት፥ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤’
የጌጥ ልብስም የለበሰውን ተመልክታችሁ “አንተስ በዚህ በመልካም ስፍራ ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ድኻውንም “አንተስ ወደዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ መረገጫ በታች ተቀመጥ፤” ብትሉት፥ ራሳችሁን መለያየታችሁ አይደለምን?