የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
ኢሳይያስ 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዳይማሩአት ሕግን የሚያጠፉአት ሰዎች ያንጊዜ ይገለጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምስክርነቱን አሽገው፤ ሕጉንም በደቀ መዛሙርቴ መካከል አትመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስክርነቱን አሽገው፤ ሕጉንም በደቀ መዛሙርቴ መካከል አትመው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምስክርነቱን ጠብቀህ ያዝ፤ በደቀ መዛሙርቴ ልብ ውስጥም ሕጉን አትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምስክሩን እሰር፥ በደቀ መዛሙርቶቼም መካከል ሕጉን አትም። |
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
ለሥጋዊ ሰው ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ይመስለዋልና፥ አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቅ አይችልም።
ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው፤ አትጻፈውም፤” የሚል ድምፅ ሰማሁ።
ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።
ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።