ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ስለ እርስዋም አልተጣሉትም፤ ስምዋንም “መርኅብ” ብሎ ጠራት፤ እንዲህ ሲል፥ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፤ በምድርም አበዛን።”
ኢሳይያስ 54:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋረጃዎችሽንም ዘርጊ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ፤ ካስሞችሽንም ትከዪ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ፤ የድንኳንሽን መጋረጃዎች በትልቁ ዘርጊ፤ ፈጽሞ አትቈጥቢ፤ ገመዶችሽን አርዝሚአቸው፤ ካስማዎችሽንም ቀብቅቢ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትኖሪበትን የድንኳንሽንም ቦታ አስፊ፤ መጋረጃዎችሽም እንዲዘረጉ አድርጊ፤ አታጥብቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ፤ ካስማዎችሽንም አጠንክሪ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፥ አትቈጥቢ፥ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። |
ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ስለ እርስዋም አልተጣሉትም፤ ስምዋንም “መርኅብ” ብሎ ጠራት፤ እንዲህ ሲል፥ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፤ በምድርም አበዛን።”
የአደባባዩንም መጋረጆች፥ ምሰሶዎቹንም፥ እግሮቹንም፥ የአደባባዩንም ደጃፍ መጋረጃ፥ አውታሮቹንም፥ ካስማዎቹንም፥ ለምስክሩ ድንኳን ማገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ፤
እነሆ፥ የመድኀኒታችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህም ድንኳኖችዋ የማይናወጡ፥ ካስማዎችዋ ለዘለዓለም የማይነቀሉ፥ አውታሮችዋም ሁሉ የማይበጠሱ፥ የበለጸገች ከተማ ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
ድንኳኔም ተበዘበዘ፤ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆችና በጎችም የሉም ከእንግዲህ ወዲህ ለድንኳኔም ቦታ የለም ለመንጎችም መሰማሪያ የለም፤