ኢሳይያስ 53:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዷልና ልደቱን ማን ይናገራል? ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ለሞት ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመትቶ፣ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ፣ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ ላይ የተዛባ ፍርድ ተወስኖበት ተወሰደ፤ የወደፊትስ ሁኔታውን ማስተዋል የሚችል ማነው? ሆኖም ስለ ሕዝቤ መተላለፍ ተመታ፤ ከሕያዋንም ዓለም ተወገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፥ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? |
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፤ ከኀያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ኀጢአታቸውም ተሰጠ።
እርሱ ግን ስለ ኀጢአታችን ቈሰለ፤ ስለ በደላችንም ታመመ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
አይሁድም መልሰው፥ “እኛ ሕግ አለን፤ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባል፤ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና” አሉት።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀይሉና በመንፈስ ቅዱስ፥ ከሙታንም ተለይቶ በመነሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤