ኢሳይያስ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፥ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል እስኪ ፍረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤ በእኔና በወይኔ ቦታ መካከል እስኪ ፍረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንት በኢየሩሳሌም የምትኖሩና የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤ በእኔና በወይኔ ቦታ መካከል እስቲ ፍረዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ወዳጄ እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! በእኔና በወይን ተክል ቦታዬ መካከል ስላለው ነገር እስቲ ፍረዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎችም ሆይ፥ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል እስኪ ፍረዱ። |
ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ ሌላ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወይንን ያፈራል ብዬ ጠበቅሁት፤ ነገር ግን እሾህን አፈራ።
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።
መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።