ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝሩ የለካ፥ ምድርንም ሁሉ ሰብስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን፥ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
ኢሳይያስ 41:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር ፊተኛውና ኋለኛው እኔ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የሠራና ያደረገ፣ ትውልድን ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር ከፊተኛው፣ ከኋለኛውም ጋራ፤ እኔው ነኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራው ማን ነው? እኔ ጌታ፥ መጀመሪያም እስከ መጨረሻውም የምኖር፥ እኔ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ እንዲሆን የፈቀደ ማን ነው? የታሪክንስ ሂደት የሚቈጣጠር ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ ነበርኩ፤ በመጨረሻም የምገኝ እኔው ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራው ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር፥ ፊተኛው በኋለኞችም ዘንድ የምኖር፥ እኔ ነኝ። |
ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝሩ የለካ፥ ምድርንም ሁሉ ሰብስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን፥ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
ዐይናችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? ከዋክብትንም በሙሉ የሚቈጥራቸው እርሱ ነው፤ በየጊዜያቸው ያመጣቸዋል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በክብሩ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
ይኸውም የእግዚአብሔር እጅ ይህን ሁሉ እንደ ሠራ፥ የእስራኤልም ቅዱስ ይህን እንደ አሳየ ያውቁ ዘንድ፥ ያስተውሉም ዘንድ፥ ይረዱም ዘንድ፥ ያምኑም ዘንድ ነው።
እናውቅ ዘንድ፥ ከጥንት የተነገረው፦ እውነት ነው እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? ከመሆኑ በፊት የሚናገር የለም፤ የሚገልጥም የለም፤ ቃላችሁን የሚሰማ የለም።
ያዕቆብን እንዲማርኩት፥ እስራኤልንም እንዲበዘብዙት ያደረገ ማን ነው? እነርሱም የበደሉት፥ በመንገዱም ይሄዱ ዘንድ ያልወደዱት፥ ሕጉንም ያልሰሙት እግዚአብሔር እርሱ አይደለምን?
ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ፥ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮች ሁኑ፤ እኔም ምስክር እሆናችኋለሁ ይላል እግዚአብሔር አምላክ፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልነበረም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም።
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
እርሱም በምድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖሩባትም ዘንድ ዘመንንና ቦታን ወስኖ ሠራላቸው።
እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም።
እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።