ኢሳይያስ 40:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ጩኽ” የሚል ሰው ቃል፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድምፅም፣ “ጩኽ” አለኝ፤ እኔም፣ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ድምጽ “ጩኽ!” አለኝ፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልኩ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ድምፅ “የዐዋጅ ቃል ተናገር!” እያለ ይጮኻል። እኔም “ምን ብዬ ላውጅ!” ስል ጠየቅሁ። ያም ድምፅ “እንዲህ ብለህ ዐውጅ” አለኝ፦ “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጩኽ የሚል ሰው ቃል፥ ምን ብዬ ልጩኽ? አልሁ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው። |
እኔ ነኝ፤ የማጽናናሽ እኔ ነኝ፤ አንቺ እንግዲህ ዕወቂ፤ ማንን ፈራሽ? የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ነውን?
በኀይልህ ጩኽ፤ አትቈጥብ፤ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፤ ለሕዝቤ ኀጢአታቸውን፥ ለያዕቆብ ቤትም በደላቸውን ንገር።
“ሂድ፤ እንዲህ ብለህ በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
በኤፍሬም ተራሮች ላይ የሚከራከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጠሩባት ቀን ትመጣለችና።”
ስለዚህም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፦ ስበክ እንዲህም በል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ በታላቅ ቅንዓት በኢየሩሳሌምና በጽዮን ቀንቻለሁ።