ኢሳይያስ 38:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እግዚአብሔር የገባልህን ቃል እንደሚፈጽምልህ፣ የእግዚአብሔር ምልክት ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታም የተናገረውን ነገር እንደሚፈጽመው ከጌታ ይህ ምልክት ይሆንልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢሳይያስም እንዲህ ሲል መለሰለት፥ “እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል የሚፈጽም ስለ መሆኑ የሚሰጥህ ምልክት ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል። |
በዚያም ቀን፦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በውስጡም ያለው ስብ ይፈስሳል” ብሎ ምልክት ሰጠ።
ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በሀገሩ ላይ ስለ ተደረገው ተአምራት ይጠይቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተላኩ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።
“ይህም ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የዘራኸውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላቸሁ፤ ታጭዱማላችሁ፤ ወይንንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።