ራፋስቂስ ግን፥ “በውኑ ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?” አላቸው።
ኢሳይያስ 36:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራፋስቂስ ግን፥ “ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ፥ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ለተቀመጡት ሰዎች እነግራቸው ዘንድ አይደለምን?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የጦር አዛዡ መልሶ፣ “ጌታዬ እነዚህን ቃሎች እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነበርን? እንደ እናንተ የራሳቸውን ኵስ ለመብላትና ሽንታቸውንም ለመጠጣት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎችም አይደለምን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራፋስቂስ ግን፦ “አለቃዬ ይህን ቃል እንድናገር ወደ እናንተና ወደ አለቃችሁ ብቻ ልኮኛልን? እንደ እናንተ የራሳቸውን ኩስ ለመብላትና ሽንታቸውንም ለመጠጣት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ጭምር አይደለምን?” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሦራውያን ባለሥልጣንም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታዬ የአሦር ንጉሥ ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣችሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? ከቶ አይደለም፤ ልክ እንደ እናንተ ዐይነ ምድራቸውን መብላትና ሽንታቸውን መጠጣት ያለባቸው ሕዝቡም ጭምር ስለ ሆኑ እኔ የምናገረውን በቅጽሩ ላይ ያሉት ሕዝቡ ሁሉ እንዲሰሙት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራፋስቂስ ግን፦ ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡ ሰዎች አይደለምን? አላቸው። |
ራፋስቂስ ግን፥ “በውኑ ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?” አላቸው።
ኤልያቄምና ሳምናስ፥ ዮአስም ራፋስቂስን፥ “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕብራይስጥ አትናገረን” አሉት።
የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።
ደግሞም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የኢየሩሳሌምን እንጀራ በትር እሰብራለሁ፤ በችግር እያሉ እንጀራን በሚዛን ይበላሉ፥ እየደነገጡም ውኃን በልክ ይጠጣሉ፤