አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
ኢሳይያስ 32:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐመፃቸው ነገር ድሃውን ይገድሉት ዘንድ፥ የድሆችንም ፍርድ ይገለብጡ ዘንድ የክፉዎች ሕሊና ዐመፅን ትመክራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋጠወጥ ዘዴ ክፉ ነው፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆን፣ ድኻን በሐሰት ለማጥፋት፣ ክፋት ያውጠነጥናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሸንጋይ ሽንገላ ክፉ ናት፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆንም እንኳን በሐሰት ቃል ድሀውን ለማጥፋት ክፉን አሳብ ያስባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባለጌዎች ሥራ ክፉ ነው፤ ምንም ያኽል የድኾች አቤቱታ ትክክል ቢሆን ውሸት በመናገር ድኾችን ለማጥፋት ክፉ ዕቅድ ያቅዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንፉግም ዕቃ ክፉ ናት፥ ችግረኛ ቅን ነገርን በተናገረ ጊዜ እንኳን እርሱ በሐሰት ቃል ድሀውን ያጠፋ ዘንድ ክፉን አሳብ ያስባል። |
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
በምድር ጽድቅን የማይማርና መልካምን የማያደርግ ኃጥእ አልቆአልና፥ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ኀጢአተኛን ያስወግዱታል።
እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፥ በበርም ለሚገሥጸው አሽክላ የሚያኖሩ፥ ጻድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱ ናቸው።
ክፉ ሰው መንገዱን፥ በደለኛም ዐሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ፤ እርሱም ይምረዋል፤ እርሱ ብዙ በደላችሁን ይተውላችኋልና።
ከእውነት ተወግደዋል፤ እንዳያስተውሉም ልባቸውን መልሰዋል። እግዚአብሔርም አየ፤ ፍርድም ስለሌለ ደስ አላለውም።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።