የበለጸገች ከተማና ቤቶችዋ ምድረ በዳ ይሆናሉ። የከተማውን ሀብትና ያማሩ ቤቶችን ይተዋሉ፤ አንባዎችም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማሪያ ይሆናሉ።
ኢሳይያስ 30:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ፥ በረዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላቁ የዕልቂት ቀን ምሽጎች ሲፈርሱ፣ በረጅም ተራራ ሁሉና ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ላይ ወራጅ ወንዝ ይፈስሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ፥ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይወርዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቡ ላይ እልቂት በሚደርስበት ጊዜ ከታላላቅ ተራራዎችና ከከፍተኛ ኰረብቶች የምንጭ ውሃ ይፈስሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ እረጅሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ። |
የበለጸገች ከተማና ቤቶችዋ ምድረ በዳ ይሆናሉ። የከተማውን ሀብትና ያማሩ ቤቶችን ይተዋሉ፤ አንባዎችም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማሪያ ይሆናሉ።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው።
በምድረ በዳም በተጠሙ ጊዜ፥ ውኃን ከዓለቱ ውስጥ ያፈልቅላቸው ነበር፤ ዓለቱም ተሰነጠቀ፤ ውኃውም ይፈስስላቸው ነበር፤ ሕዝቤም ይጠጡ ነበር።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከረዥሙ ዝግባ ጫፍ ላይ ቀንበጥን ወስጄ አኖረዋለሁ፤ ከጫፎቹም አንዱን ቀንበጥ እቀነጥበዋለሁ፤ በረዥምና በታላቅ ተራራም ላይ እተክለዋለሁ።
ከአሕዛብም ዘንድ አወጣቸዋለሁ፤ ከሀገሮችም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገዛ ሀገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾችም አጠገብ፥ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩባት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።
እነርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ስፍራዎች እባርካቸዋለሁ፤ ዝናቡንም በጊዜው አወርዳለሁ፤ የበረከትም ዝናብ ይሆናል።
ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።
“በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች ማርን ያንጠባጥባሉ፤ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ፤ በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት ምንጭ ትፈልቃለች፤ የሰኪኖንንም ሸለቆ ታጠጣለች።