ኢሳይያስ 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር የእግር አልቦውን ክብር፥ መርበቡንም፥ ጨረቃ የሚመስለውንም ጌጥ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ቀን ጌታ የክብር ጌጣቸውን ይነጥቃቸዋል፤ የእግር አንባሩን፣ የጠጕር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን የዐንገት ጌጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ጌታ የክብር ጌጣቸውን ይነጥቃቸዋል፤ የእግር አንባሩን፤ የጠጉር ጌጡን፤ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን የዐንገት ጌጥ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን ጌታ የኢየሩሳሌምን ሴቶች ጌጣጌጥ ማለት የእግራቸውን አልቦ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ የአንገታቸውን ጌጣጌጥ፥ የጆሮአቸውን ጒትቻ፥ አምባራቸውን፥ የፊታቸውን መሸፈኛ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ፥ በክንዳቸው ላይ የሚያደርጉትን ጌጥ፥ በወገባቸው ላይ የሚያስሩትን መቀነት፥ የሽቶ ጠርሙሳቸውን፥ ጥንቈላ የተጻፈበትን አሸንክታብ፥ የጣታቸውንና የአፍንጫቸውን ቀለበት፥ ለዓመት በዓል የሚሆነውን የክት ልብስ፥ መጐናጸፊያቸውንና ካባቸውን፥ የእጅ ቦርሳቸውን፥ መስታዋታቸውን፥ ከሐር የተሠራ የውስጥ ልብሳቸውን፥ ራስ ማሰሪያቸውንና ዐይነ ርግባቸውን ሁሉ ያስወግዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ጌታ የእግር አልቦውን ክብር፥ መርበብንም፥ ጨረቃ የሚመስለውንም ጌጥ፥ |
ከሩቅ ሀገርም ወደመጡ ሰዎች መልእክተኞችን ላኩ፤ እነርሱም በደረሱ ጊዜ ይታጠባሉ፤ ዐይኖቻቸውንም ይኳላሉ፤ ያጌጣሉም።
ዛብሄልና ስልማናም፥ “ኀይልህ እንደ ጐልማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነሥተህ ውደቅብን” አሉት። ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደለ፤ በግመሎቻቸውም አንገት የነበሩትን ሥሉሴዎች ማረከ።
የለመነውም የወርቅ ጕትቻ ሚዛኑ ከአምባሩ፥ ከድሪውም፥ የምድያምም ነገሥታት ከለበሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ሥሉሴዎች ሌላ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ።