La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 29:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰዎች ተር​በው ሌሊት በሕ​ል​ማ​ቸው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ጣ​ሉም፤ በተ​ነሡ ጊዜ ግን ሕል​ማ​ቸው ከንቱ ነው። የተ​ጠማ ሰውም እን​ደ​ሚ​ጠጣ ያል​ማል፤ በነ​ቃም ጊዜ እንደ ተጠማ ነው፤ ነፍ​ሱም በከ​ንቱ ትመ​ኛ​ለች። ደብረ ጽዮ​ንን የሚ​ዋጉ የአ​ሕ​ዛብ ብል​ጽ​ግ​ናም እን​ደ​ዚሁ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ ራቡ እንዳልለቀቀው፣ የጠማውም ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ እንደ ዛለና ጥማቱም እንዳልተወው፣ የጽዮንን ተራራ የሚወጋ፣ የአሕዛብ መንጋ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ተርቦም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፤ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይበላል፥ ነገር ግን ይነቃል ሰውነቱም ባዶ ነው፤ ተጠምቶም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፤ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይጠጣል፥ ነገር ግን ይነቃል፥ እነሆም፥ ይዝላል ሰውነቱም እንደተጠማ አለ፤ የጽዮንን ተራራም የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደዚሁ ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ በመጣል የተሰበሰቡ መንግሥታት ሁሉ በሕልሙ ሲበላ ዐድሮ ጠዋት በነቃ ጊዜ ምንም ያልቀመሰ ረኃብተኛ መሆኑንና እንዲሁም በሕልሙ ሲጠጣ ዐድሮ ጧት በነቃ ጊዜ ጒሮሮው በውሃ ጥም ደርቆ እንደሚያገኘው ሰው ይሆናሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ተርቦም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፥ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይበላል፥ ነገር ግን ይነቃል ሰውነቱም ባዶ ነው፥ ተጠምቶም እንደሚያልም ሰው ይሆናል፥ በሕልሙም፥ እነሆ፥ ይጠጣል፥ ነገር ግን ይነቃል፥ እነሆም፥ ይዝላል ሰውነቱም አምሮት አለው፥ እንዲሁም የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 29:8
10 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አ​ኩን ላከ፤ እር​ሱም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን አለ​ቆ​ቹ​ንም ከአ​ሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ። ወደ አም​ላ​ኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወ​ገቡ የወ​ጡት ልጆቹ በዚያ በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።


አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነፍሴ በሕ​ግህ ታገ​ሠች።


ወደ ኪዳ​ን​ህም ተመ​ል​ከት፥ የም​ድር የጨ​ለማ ስፍ​ራ​ዎች በኃ​ጥ​ኣን ቤቶች ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


እነሆ፥ የሚ​ቃ​ወ​ሙህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ እን​ዳ​ል​ነ​በ​ሩም ይሆ​ናሉ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህም ይጠ​ፋሉ።


የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​ህ​ንም ሰዎች ትሻ​ቸ​ዋ​ለህ፤ አታ​ገ​ኛ​ቸ​ው​ምም፤ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ይሆ​ና​ሉና፤ የሚ​ዋ​ጋ​ህም የለም።


ብረት ሠሪ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ውን ይስ​ላል፤ ጣዖ​ቱን በመ​ጥ​ረ​ቢያ ይቀ​ር​ጸ​ዋል፤ በመ​ዶ​ሻም መትቶ ቅርጽ ይሰ​ጠ​ዋል፤ በክ​ን​ዱም ኀይል ይሠ​ራ​ዋል፤ እር​ሱም ይራ​ባል፤ ይደ​ክ​ም​ማል፤ ውኃም አይ​ጠ​ጣም።


በአ​ንቺ ላይ የተ​ሠራ መሣ​ሪያ ሁሉ እን​ዲ​ከ​ና​ወን አላ​ደ​ር​ግም፤ በአ​ንቺ ላይ ለፍ​ርድ የሚ​ነ​ሣ​ውን ድምፅ ሁሉ ታጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ጠላ​ቶ​ች​ሽም ሁሉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ርስት አላ​ቸው፤ ጻድ​ቃ​ኔም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።


የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቶአል፣ ምሽግን ጠብቅ፥ መንገድንም ሰልል፣ ወገብህን አጽና፥ ኃይልህንም እጅግ አበርታ።