ኢሳይያስ 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩንም ለማጽናት ቤቶችን አፈረሳችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጠራችሁ፥ ቅጥሩንም ለመጠገን ቤቶችን አፈረሳችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ሁሉ እየተዘዋወራችሁ ቈጠራችሁ፤ ቅጥሩን ለማደስ አንዳንዶቹን ቤቶች አፈረሳችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጠራችሁ፥ ቅጥሩንም ለማጥናት ቤቶችን አፈረሳችሁ። |
በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፤ ቀድሞ የሠራውንም አላያችሁም።
እግዚአብሔርም ኢሳይያስን አለው፥ “አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው መታጠቢያ ቦታ ውጡ፤
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለምሽግና ለመከላከያ ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦