ኢሳይያስ 15:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ኢሊም ጕድጓድ ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤ ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣ ሰቈቃቸውም እስከ ብኤርኢሊም ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጩኸት በሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ያስተጋባል፤ ዋይታም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሞአብ ጠረፎች በየስፍራው ጩኸት ይሰማል፤ ጩኸቱም እስከ ኤግላይምና እስከ ብኤርኤሊም ደርሶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፥ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ። |
የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ በዲሞን ላይ ዐረባውያንን አመጣለሁና፤ የሞዓብንና የአርያልን ዘር፥ ከኤዶምያስም የተረፉትን ወስጄ እንደ አራዊት በምድር ላይ እሰድዳቸዋለሁ።
ዓሣ አጥማጆችም ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ በዚያ ይቆማሉ። ያም መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።