ዕብራውያን 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመላእክትህ ጥቂት አሳነስኸው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድንም ጫንህለት፤ በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አሳነስኸው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፤ በእጆችህም ሥራ ላይ ሾምከው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥቂት ከመላእክት አሳነስከው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፥ በእጆችህም ሥራ ላይ ሾምከው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አሳነስኸው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት፥ በእጆችህም ሥራ ላይ ሾምኸው፤ |
በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ጭኖ እናየዋለን።