እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ፥ ከባድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
ዕብራውያን 12:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የታያቸውም እንዲህ ግሩም ነበር፤ ሙሴም እንኳን፥ “እኔ ፈርቻለሁ፥ ደንግጫለሁም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ይታይ የነበረውም ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነበርና፣ ሙሴ “በፍርሀት ተንቀጠቀጥሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም “እጅግ እፈራለሁ፤ እንቀጠቀጥማለሁ፤” እስኪል ድረስ የሚታየው ነገር እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታየው ድርጊት እጅግ አስፈሪ ከመሆኑ የተነሣ ሙሴ እንኳ “እኔ ፈራሁ፤ ተንቀጠቀጥኩም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም፦ እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ |
እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ፥ ከባድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።