ፈርዖንም ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፤ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ ወደ ምድያም ምድር በደረሰ ጊዜም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።
ዕንባቆም 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፣ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣ የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢትዮጵያ ድንኳኖች በጭንቀት ላይ ሆነው አየሁ፥ የሚድያን ምድር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢትዮጵያ ሰፈር ሲጨነቅ፥ የምድያምም ሰዎች ሲንቀጠቀጡ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፥ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ። |
ፈርዖንም ይህን ነገር ሰማ፤ ሙሴንም ሊገድለው ፈለገ። ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኰበለለ፤ በምድያምም ምድር ተቀመጠ፤ ወደ ምድያም ምድር በደረሰ ጊዜም በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ዐረፈ።
ድንኳናቸውንና በጎቻቸውን ይወስዳሉ፤ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ፥ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፤ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው።
ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት፥ እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
መልሰውም ኢያሱን፥ “እኛ ባሪያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ ይሰጣችሁ ዘንድ፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ ያጠፋ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፤ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ፈራን፤ ይህንም ነገር አድርገናል፤
ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፤ እርሱም አሳደዳቸው፤ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዘ፤ ጌዴዎንም ሠራዊቱን ሁሉ አጠፋ።