ዕንባቆም 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታላላቅ ውሆችን በመናጥ፣ ባሕሩን በፈረሶችህ ረገጥህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፈረሶችህ በባሕር ላይ ተራመድህ፥ ብዙ ውኆችንም ረገጥህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ባሕሩን በፈረሶችህ በምትረጋግጥበት ጊዜ ጥልቁ ባሕር ይናወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ። |
በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።