እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፥ “ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ሁሉ፥ ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ሁን ፤ በደረትህና በሆድህም ትሄዳለህ፤ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ።
ዘፍጥረት 9:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኖኅም እንዲህ አለ፥ “ከነዓን ርጉም ይሁን፤ ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹም የባርያዎች ባርያ ይሁን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አለ፤ “ከነዓን የተረገመ ይሁን! ለወንድሞቹ የአገልጋዮች አገልጋይ ይሁን፤ እንደገናም እንዲህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለ፥ ከነዓን ርጉም ይሁን ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን። |
እግዚአብሔር አምላክም እባቡን አለው፥ “ይህን ስላደረግህ ከእንስሳት ሁሉ፥ ከምድር አራዊትም ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ሁን ፤ በደረትህና በሆድህም ትሄዳለህ፤ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ አፈርን ትበላለህ።
ቍጣቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበርና፤ ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፤ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢኣትን የሚሠራ ሁሉ የኀጢኣት ባርያ ነው።
አሁንም የተረገማችሁ ሁኑ፤ ለእኔም፥ ለአምላኬም እንጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእናንተ አይጠፋም” አላቸው።
በዚያም ቀን ኢያሱ እነርሱን ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው። ስለዚህም የገባዖን ሰዎች ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ እግዚአብሔርም ለመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ቈራጮች፥ ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።