እግዚአብሔርም የምድር አራዊትን እንደየወገኑ፥ እንስሳትንም እንደየወገኑ፥ በምድር የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ እንደየወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ዘፍጥረት 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕይወት እስትንፋስ ያለው ሁሉ፥ በየብስም ያለው ሁሉ ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአፍንጫቸው የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው በየብስ የነበሩ ፍጥረታት ሁሉ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ የሚኖር የሕይወት እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ላይ የሚኖር እስትንፋስ ያለው ነገር ሁሉ ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየብስ የነበረው በአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ። |
እግዚአብሔርም የምድር አራዊትን እንደየወገኑ፥ እንስሳትንም እንደየወገኑ፥ በምድር የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ እንደየወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።