ዘፍጥረት 6:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሚበላውም የመብል ዓይነት ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተ ትሰበስባለህ፤ እርሱም ለአንተ፥ ለእነርሱም መብል ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአንተና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ አከማች።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሚበላውም መብል ሁሉ ለአንተ ውሰድ፤ ወደ አንተም ትሰበስባለህ እርሱም ለአንተም ለእነርሱም መብል ይሆናል። |
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?