ዘፍጥረት 46:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፥ “እኔ ሄጄ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞችና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ አናግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እኔ መጥቼ ለፈርዖን፦ ‘እንግዲህ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤት ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የቀረውን የአባቱን ቤተሰብ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ልሂድና ‘በከነዓን ምድር ይኖሩ የነበሩት ወንድሞቼና የቀሩትም የአባቴ ቤተሰቦች ወደ እኔ መጥተዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ስዎች እንዲህ አላቸው፦ እኔ መጥቼ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤ |
እነርሱን የቀደሳቸው እርሱ፥ የተቀደሱት እነርሱም ሁሉም በአንድነት ከአንዱ ናቸውና። ስለዚህም እነርሱን፥ “ወንድሞች” ማለትን አያፍርም።