ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
ዘፍጥረት 43:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እህል እንሸምትበት ዘንድ ሌላም ብር በእጃችን አመጣን፤ ብራችንንም በዓይበታችን ማን እንደ ጨመረው አናውቅም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እህል መሸመቻ የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ ያኔ ገንዘቡን በየስልቾቻችን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እህል መሸመቻ የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ ያኔ ገንዘቡን በየስልቾቻችን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን እህል የምንሸምትበትንም ገንዘብ በተጨማሪ ይዘናል፤ በዚያን ጊዜ ገንዘባችንን መልሶ በየስልቻዎቻችን ማን እንደ ከተተው አናውቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እህል እንሽምትበር ዘንድ ሌላም ብር በእጃችን አመጣን ብራችንንም በዓይበታችን ማን እንደ ጨመረው አናውቅም። |
ከእነርሱም አንዱ በአደሩበት ስፍራ ለአህዮቹ ገፈራን ይሰጥ ዘንድ ዓይበቱን ፈታ፤ ብሩንም በዓይበቱ አፍ ተቋጥሮ አገኘ።
ብሩን በአጠፌታ አድርጋችሁ በእጃችሁ ውሰዱ፤ በዓይበታችሁም አፍ የተመለሰውን ብር መልሳችሁ ውሰዱ፤ ምናልባት ባለማወቅ ይሆናል።
እንዲህም ሆነ፥ ወደምናድርበትም ስፍራ በደረስን ጊዜ ዓይበታችንን ከፈትን፤ እነሆም፥ የየአንዳንዱ ሰው ብር በየዓይበቱ አፍ ነበር፤ አሁንም ብራችንን በእጃችን እንደ ሚዛኑ መለስነው።
እርሱም አላቸው፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ አምላካችሁ የአባቶቻችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁንስ መዝኜ ተቀብያለሁ።”