ዘፍጥረት 42:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የሰላም ሰዎች ነን፤ ባሪያዎችህስ ሰላዮች አይደሉም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የምንታመን ነን፤ ሰላዮችም አይደለንም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እና ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን እኛ እውነተኞች ነን ባሪያዎችህስ ሰላዩች አይደሉም |
ወንድማችሁን ያመጣ ዘንድ ከእናንተ አንዱን ላኩ፤ እናንተ ግን እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ወይም ከአልሆነ ነገራችሁ እስኪታወቅ ድረስ ከዚህ ተቀመጡ፤ ይህ ከአልሆነ ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ሰላዮች ናችሁ።”
እናንተ ሰላማውያን ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞት ቤት ይታሰር፤ እናንተ ግን ሂዱ፤ የሸመታችሁትን እህልም ውሰዱ፤
እነርሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትውልዳችን ፈጽሞ ጠየቀን፤ እንዲህም አለን፦ ‘ሽማግሌው አባታችሁ ገና በሕይወት ነው? ወንድምስ አላችሁን?’ እኛም እንደዚሁ እንደ ጠየቀን መለስንለት፤ በውኑ፦ ‘ወንድማችሁን አምጡ’ እንዲለን እናውቅ ነበርን?”
ነገር ግን በሁሉ ራሳችንን አቅንተን፥ የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንሁን፤ በብዙ ትዕግሥትና በመከራ፥ በችግርና በጭንቀት ሁሉ፥