የያዕቆብም ትውልድ እንዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ እርሱም ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላቴና ነበረ፤ ዮሴፍም የክፋታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው ወደ እስራኤል ያመጣ ነበር።
ዘፍጥረት 41:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፥ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብጽን ምድር በሙሉ ዞረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ ዮሴፍ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ በመላው የግብጽ ምድር በመዘዋወር ጒብኝት ያደርግ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። |
የያዕቆብም ትውልድ እንዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ እርሱም ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላቴና ነበረ፤ ዮሴፍም የክፋታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው ወደ እስራኤል ያመጣ ነበር።
እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በምድር ላይ ራብ የሆነበት ነውና፤ የማይታረስበትና የማይታጨድበት አምስት ዓመት ገና አለ።
ንጉሡም ሮብዓም፥ “ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድን ነው?” ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ።
ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትለያለህ።