ደግሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመጣል፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ የነበረውንም ጥጋብ ሁሉ ይረሱታል፤ ራብም ምድርን ሁሉ ያጠፋል፤
ዘፍጥረት 41:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላም ከሚሆነው ከዚያ ራብ የተነሣ በምድር የሆነው ጥጋብ አይታወቅም፤ እጅግ ጽኑ ይሆናልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥጋቡ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፥ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተከታዩ የራብ ዘመን እጅግ አሠቃቂ ስለሚሆን የጥጋብ ጊዜ ፈጽሞ እንዳልነበረ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኍላ ከሚሆነው ከዚያ ራብ የተነሣም በምድር የሆነው ጥጋብ አያታወቅም እጅግ ጽኑ ይሆናልና። |
ደግሞም ከዚህ በኋላ ሰባት የራብ ዓመት ይመጣል፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ የነበረውንም ጥጋብ ሁሉ ይረሱታል፤ ራብም ምድርን ሁሉ ያጠፋል፤
ሕልሙም ለፈርዖን ደጋግሞ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለሆነ ነው፤ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ያደርገዋል።
ምድር በወይን እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ ሕግን መተላለፍዋም ይከብድባታል፤ ትወድቅማለች፤ ደግማም አትነሣም።
የእግዚአብሔርም እጅ በአዛጦን ሰዎች ላይ ከበደች፤ ክፉም ነገር አመጣችባቸው፤ በእነርሱም ላይ በመርከቦች ውስጥ ወጣ፤ የአዛጦንንና የአውራጃዎችዋንም ሰዎች የውስጥ አካላቸውን በዕባጭ መታ፤ በከተሞቻቸውም መካከል አይጦች ወጡ፤ በከተማውም ታላቅ መቅሠፍት ሆነ።