እነዚያ ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እነዚያም ሰባቱ መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው።
ዘፍጥረት 41:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በኋላ የወጡት እነዚያ የከሱና መልከ ክፉዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እነዚያም የሰለቱትና ነፋስ የመታቸው ሰባቱ እሸቶች እነርሱ ራብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም በኋላ የወጡት ሰባት የከሱትና አስከፊዎቹ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ እንዲሁም ሰባቱ የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው፤ ይኸውም ሰባት የራብ ዓመቶች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በኍላ የወጡት የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ የሰለቱትና የምሥራቅ ነፋስ የመታቸው ሰባቱም እሽቶች እነርሱ ራብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ናቸው። |
እነዚያ ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እነዚያም ሰባቱ መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው።
ከእነርሱም በኋላ እነሆ፥ መልካቸው የከፋ፥ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ተሰማርተው ነበር።
ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሣላትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር በምድር ራብን ጠርቶአልና፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይቆያል” ብሎ ተናገራት።