Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 41:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እነ​ዚያ ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች እሸ​ቶች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሰባቱ የሚያማምሩ ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ ሰባቱም ያማሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው ሕልሙ አንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 41:26
15 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።


ዮሴ​ፍም አለው፥ “የሕ​ል​ምህ ትር​ጓ​ሜው ይህ ነው፤ ሦስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ሦስት ቀኖች ናቸው።


ዮሴ​ፍም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “የሕ​ል​ምህ ትር​ጓ​ሜው ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤


እነ​ሆም፥ መል​ካ​ቸው ያማረ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የወ​ፈረ ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በወ​ን​ዙም ዳር በመ​ስኩ ይሰ​ማሩ ነበር።


ዮሴ​ፍም ፈር​ዖ​ንን አለው፥ “የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​ይ​ቶ​ታል።


ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው።


እነሆ፥ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ይመ​ጣሉ፤


በሰ​ባ​ቱም የጥ​ጋብ ዓመ​ታት ግብፅ ያስ​ገ​ኘ​ችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ።


ደግ​ሞም ተኛ፤ ሁለ​ተኛ ሕል​ም​ንም አየ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ንድ አገዳ ላይ የነ​በሩ፥ ያማ​ሩና ምርጥ የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤


በግ​ብፅ ምድር የነ​በ​ረ​ውም ሰባቱ የጥ​ጋብ ዓመት አለፈ፤


ወገ​ቦ​ቻ​ች​ሁን ታጥ​ቃ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ ተጫ​ም​ታ​ችሁ፥ በት​ራ​ች​ሁ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ይዛ​ችሁ እን​ዲህ ብሉት፦ እየ​ቸ​ኰ​ላ​ች​ሁም ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ፤ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነውና።


አምሳ የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎች ሥራ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ ድን​ኳ​ኑም አንድ ይሆ​ናል።


ሁሉም ያን መን​ፈ​ሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይኸ​ውም በኋ​ላ​ቸው ከሚ​ሄ​ደው ከመ​ን​ፈ​ሳዊ ዐለት የጠ​ጡት ነው፤ ያም ዐለት ክር​ስ​ቶስ ነበረ።


መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos