ከዚህ ነገር በኋላም እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አበዛዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፅ ንጉሥን በደሉ።
ዘፍጥረት 40:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በዕንጨት ላይ ሰቀለው፤ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንጀራ ቤት ኀላፊውን ግን እንዲሰቀል አደረገው፤ ሁሉም ነገር ዮሴፍ የእያንዳንዳቸውን ሕልም እንደ ተረጐመው ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ ሰቀለው ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው። |
ከዚህ ነገር በኋላም እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አበዛዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፅ ንጉሥን በደሉ።
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ይቈርጥሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ የሰማይ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”
እነርሱም፥ “ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን” አሉት። ዮሴፍም አላቸው፥ “ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ፤ ሕልማችሁ ምንድን ነው?”
የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር።