ሌቦች በስውር ከዕብራውያን ሀገር ሰርቀውኛልና፤ በዚህም ደግሞ ምንም ያደረግሁት ሳይኖር በግዞት ቤት አኑረውኛልና።”
ዘፍጥረት 40:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእንጀራ አበዛዎቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጐመለት በአየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፥ “እኔም ደግሞ ሕልም አይች ነበር፤ እነሆም፥ ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም፣ የተሰጠው ፍች ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፤ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእንጀራ ቤት አዛዡም፥ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም፥ የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፥ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፤ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንጀራ ቤት ኀላፊውም ዮሴፍ ለወይን ጠጅ አሳላፊው ሕልም የሰጠው ትርጒም መልካም መሆኑን ባየ ጊዜ፥ የእርሱንም ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ብሎ ነገረው፤ “እኔም በበኩሌ ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ ‘ሦስት መሶብ እንጀራ በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንጀራ አበዛቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጎመ ባየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ እኔም ደግሞ ሕልም አይቼ ነበር እነሆም ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤ |
ሌቦች በስውር ከዕብራውያን ሀገር ሰርቀውኛልና፤ በዚህም ደግሞ ምንም ያደረግሁት ሳይኖር በግዞት ቤት አኑረውኛልና።”
በላይኛውም መሶብ ፈርዖን የሚበላው ጋጋሪው በያይነቱ የሠራው መብል ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር።”