ዘፍጥረት 38:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን ዐወቀ፤ ወደ ወንድሙ ሚስትም በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይተካ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋራ ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወልድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፥ ከወንድሙ ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦናን የሚወለዱት ልጆች የእርሱ ያለመሆናቸውን በማወቁ ወደ ወንድሙ ሚስት ሲገባ ዘሩን ወደ ምድር ያፈሰው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በወንድሙ ስም ልጆች እንዳይወለዱ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይስጥ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር። |
“ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፤ ከእርስዋም ጋር ይኑር።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፣ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ አላቸው።