ዘፍጥረት 36:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሳውም የመሳፍንቱ ስም በየነገዳቸው፥ በየስፍራቸው፥ በያገራቸውና በየሕዝባቸው ይህ ነው፤ ትምናዕ መስፍን፥ ዓልዋ መስፍን፥ ኤቴት መስፍን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው፥ በስፍራቸውም፥ በስማቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚከተሉትም የዔሳው ዘር የነገድ አለቆች በየጐሣቸው ስምና በየሚኖሩበት ቦታ ስም ይጠራሉ፤ ቲምናዕ፥ ዐልዋ፥ ዬቴት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዔሳውም የአለቆቹ ስም በወገናቸው በስፍራቸው በስማቸውም ይህ ነው ቲምናዕ አለቃ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፤ |
የአክቦር ልጅ በአልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስቱም የሜዛአብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ምኤጠብኤል ትባላለች።