ያዕቆብም ልጁን ዲናን የኤሞር ልጅ እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም ልጆቹ እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ።
ዘፍጥረት 34:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሴኬም አባት ኤሞር፣ ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሴኬም አባት ሐሞር፥ ያዕቆብን ለማነጋገር ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ ወጣ። |
ያዕቆብም ልጁን ዲናን የኤሞር ልጅ እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም ልጆቹ እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ።
የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
የአቤድም ልጅ ገዓል፥ “አቤሜሌክ ማን ነው? እንገዛለትስ ዘንድ የሴኬም ልጅ ማን ነው? እርሱ የይሩበኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ጠባቂ አይደለምን? ከሴኬም አባት ከኤሞር ሰዎች ጋርስ አገልጋዩ አይደለምን? ስለምንስ ለዚህ እንገዛለን?