ዘፍጥረት 34:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፤ በምድራችን ይቀመጡ፤ ይነግዱባትም፤ እነሆም፥ ምድሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆቻቸውን ለሚስትነት እንውሰድ፤ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ወዳጆቻችን ናቸው፤ በአገራችን እንዲኖሩ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ያገባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፥ በምድራችን ይቀመጡ፥ ይነግዱባትም፥ እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት፥ ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ፥ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፤ በምድሪቱ ላይ አብረውን ይቀመጡ፤ በነጻም ይዘዋወሩባት፤ እነሆ፥ ምድሪቱ ለእኛም ለእነርሱም ትበቃናለች፤ የእነርሱን ሴቶች ልጆች እናግባ፤ የእኛንም ሴቶች ልጆች እንዳርላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩ፦ እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው በምድራችን ይቀመጡ ይነግዱባትም እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻቸንን እንስጥ |
እነርሱ እንደ እኛ ይሆኑ ዘንድ በዚህ ብቻ እንምሰላቸው። አንድ ወገንም እንሁን፤ እነርሱ እንደሚገርዙ ወንዶቻችንን ሁሉ እንገርዛለን።
ታናሹንም ወንድማችሁን አምጡልኝ፤ ሰላማውያን እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም በዚህ ዐውቀዋለሁ፤ ወንድማችሁንም እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በሀገራችን ትነግዳላችሁ።’ ”