ዘፍጥረት 33:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕቁባቶቹንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ፤ ልያንና ልጆችዋን በኋላ፥ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኋላ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውንም ከፊት አደረገ፥ ልያንና ልጆችዋንም አስከተለ፥ ከዚያም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን አስቀደመ፤ ቀጥሎ ልያንና ልጆችዋን አስከተለ፤ በመጨረሻም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎችንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ ልያንና ልጆችዋንም በኋለኛው ስፍራ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኍላ አደረገ። |
ያዕቆብም ዐይኑን አነሣ፤ እነሆም፥ ዔሳውን ሲመጣ አየው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ዕቁባቶቹ አደረጋቸው፤
ያዕቆብም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወድደው ነበር፤ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና። በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።
እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች፤ እነሆ በአሕዛብ መካከል ኋለኛዪቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረሀም ትሆናለች።
እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።